የአማኑኤል የልማት ድርጅት የዋጋ ግምታቸው 638,680,00 ብር የሚያወጡ የመማሪያ ግብዓቶች ድጋፍ አደረገ፡፡
 
(ቀን መጋቢት 18/2016 ዓ.ም) የአማኑኤል የልማት ድርጅት የዋጋ ግምታቸው 638,680,00 ብር የሚያወጡ አስር 43 ኢንች ስማርት ቴሌቪዥን ፤ 140 ዋይት ቦርድ ፤ 50 እሽግ ማርከር ፤ 5 እሽግ የብሬል መጻፊያ ወረቀት እና 23 እሽግ ክላስተር የመማሪያ ግብዓት ለአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ድጋፍ አደረጓል፡፡
የስፖንሰርሺፕ አስተባባሪ የሆኑት አቶ እዩኤል ቀጸላ የልማት ድርጅቱ ከክ/ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ፤ ከፋይናንስና ከሴ/ህ/ማ/ጉዳይ ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን በክ/ከተማው ውስጥ የሚገኙ የቅድመ መደበኛ ት/ቤቶች ያለባቸውን ክፍተት ለመሙላት ፕሮጀክት ቀርጾ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው የተደረገው ድጋፍ ት/ቤቶቹን ለማጠናከር ፤ የመማር ማስተማር ስራውን ምቹ ለማድረግ እና በአዲሱ የት/ት መዋቅር ት/ቤቶች እስታንዳርድ እንዲያሙዋሉ ለማገዝ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
May be an image of 2 people and text
የክ/ከተማው ትምህረት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ከበደ ዲሪባ በትምህርት ለትውልድ የንቅናቄ ተግባር በክ/ተማው ውስጥ ለሚገኙ 57 የቅድመ መደበኛና 1ኛ ደረጃ ት/ቤቶችን ያለባቸውን የግብዓት እጥረትና እስታንዳርዳቸውን ለማሟልት ከባለሀብቱ ፤ መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማትና ከማህበረሰቡ ሀብት የማሰባሰብ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝና የአማኑኤል የልማት ድርጅት ያደረገውም ድጋፍ የዚሁ አንድ አካል እንደሆነ ጠቅሰው የተደረገውንም ድጋፍ ለ10 ትምህርት ቤቶች የማሰራጨት ስራ እንደተሰራ መግለፃቸውን ከክፍለ ከተማው ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
Website: - aaceb.gov.et
Email;- This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.